Welcome to MC311 Customer Services

ኤምሲ311 (MC311) የደንበኛ አገልግሎት ማዕከል የሞንትጎመሪ ካውንቲ አስቸኳይ ያልሆኑ የመንግስት መረጃ እና የአገልግሎቶች ምንጭ ነው። በካውንቲው ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ከ7 ኤኤም እስከ 7 ፒኤም ወደ 311 በመደወል፡ ከማንኛውም ሌላ ቦታ ደግሞ ወደ  240-777-0311 በመደወል MC311 ን ማግኘት ይችላሉ። በዚህ ገፅ ያሉትን አገናኞች ይጠቀሙ፡ ወይም በ twitter @ 311MC311 ይከተሉን።

የትርጉም እርዳታ

ከእንግሊዝኛ ውጭ በሌላ ቋንቋ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ጋር ለመስራት የሚመርጡ ደንበኞች የትርጉም እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ። የኤምሲ311 (MC311) የደንበኛ አገልግሎት ማእከል ከ 150 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የቋንቋ ትርጉም አገልግሎት ይሰጣል። ወደ311 ሰደውሉ፡ ለስፓኒሽ (2) ይጫኑ፡ ካልሆነ የሚቀጥለውን የደንበኛ አገልግሎት ተወካይ በመረጡት ቋንቋ እንዲደውሉለት ለመጠየቅ መስመር ላይ ይቆዩ። የእኛ የትርጉም አገልግሎት ይቀርብልዎታል።

ድረ-ገጹን በመረጡት ቋንቋ ለመመልከት በዚሁ ገጽ በታችኛው ክፍል ያለውን የጉግል (Google) ትርጉምን ይጠቀሙ።

  • ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQ)
  • የፓልም ካርድ


ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQ)

  • ጥ፡ 311 ምንድነው?
  • መ፡ 311 የመንግስት ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚረዳ የሞንትጎመሪ ካውንቲ አዲስ የመንግስት ስልክ ቁጥር ነው።
  • ጥ፡ መረጃ እና አገልግሎትን ለማግኘት ወደ ኦንላይን (ኢንተርኔት) መሄድ እችላለሁ?
  • መ፡ አዎ፡ ወደ www.mc311.com ይሂዱ። 24/7 ይገኛል።
  • ጥ፡ የፖሊስ: የእሳት አደጋ ወይም የሕክምና አስቸኳይ ጥሪዎች እንዴት ይካሄዳሉ?
  • መ፡ ወደ 311 ቢሮ የሚወጣ ጥሪ አስቸኳይ ሁኔታን የሚመለከት ጥሪ ሆኖ ከተገኘ፡ጥሪው ወዲያውኑ ወደ 911 ኦፕሬተር ይተላለፋል፡ እናም የ 311 የደንበኞች አገልግሎት ተወካይ ደዋዩ በትክክል የተገናኘ መሆኑን ለማረጋገጥ መስመር ላይ ይቆያል። ለአስቸኳይ ጊዜያዊ መጠለያ፡የአእምሮ ጤንነት፡ የቤት ውስጥ ግጭት ወይም የልጅ ወይም የአዋቂ ጥቃት የመሳሰሉ አጣዳፊ ጉዳዮች፡ ደዋዩ ወዲያውኑ ወደ ክራይዝስ ሴንተር በ 240-777-4000 ይዛወራል።
  • ጥ፡ ለምን 311?
  • መ፡ የካውንቲ ዲፓርትመንቶችን እና አገልግሎቶችን ለመድረስ ቀላል ያደርገዋል እናም በኦንላይን (ኢንተርኔት) የሚገኝ መረጃን በእጅጉ ያሰፋዋል.
  • ጥ፡ጥ፡ ከካውንቲው ውጪ ብሆንስ፡ 311ን መድረስ እችላለሁኝ?
  • A. አዎ፡ ወደ 240-777-0311 በመደወል።
  • ጥ፡ በሞባይል ስልኬ ወደ 311 ነጻ ነው?
  • መ፡ ክፍያዎ ስለሚለዋወጥ የአገልግሎት አቅራቢዎን ይጠይቁ፡፡ አንዳንዶቹ ነጻ ሊሆኑ ሲችሉ፡ ሌሎች ሊያስከፍሉ ይችላሉ።
  • ጥ፡ የ 311 ጥሪ ማዕከል የሚሰራባቸው ሰዓቶች የትኞች ናቸው?
  • መ፡ የደንበኛ አገልግሎት ማዕከል ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 7 ሰዓት እስከ ምሽቱ 7 ሰዓት ክፍት ነው። የኦንላይን አገልግሎት በማንኛውም ጊዜ፡ ቀን ወይም ማታ በ www.mc311.com ይገኛል።
  • Q. 311 ላይ ስደውል ምን ይከሰታል?
  • መ፡ ወደ MC311 እንኳን ደህና መጣችሁ የሚል እና የሚፈልጉትን ቋንቋ እንዲመርጡ የሚጠይቅዎት አጭር ማስታወቂያ ይሰማሉ። ከዚያ በኋላ እርስዎን ለማገዝ የሰለጠነ እና እውቀተኛ እውቀት ያለው ባለሙያ ጋር ተገናኝተው እንዲገናኙ ይደረጋል። የደንበኛ አገልግሎት ማእከል በብዙ ቋንቋዎች አገልግሎት ይሰጣል እናም የመስማት ችግር ያለባቸውን የሚያግዝ  (TDD / TTY) ያካተተ ነው።
  • ጥ፡ ወደ 311ን መገናኘ መደወል ያለብኝ መቼ ነው?
  • መ፡ ስለሞንትጎመሪ ካውንቲ አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞች መረጃ ከፈለጉ፡ አገልግሎቶችን ማግኘት ከፈለጉ ወይም ለካውንቲው ባለስልጣኖች ቅሬታ ወይም ምስጋና ማቅረብ ከፈለጉ፡ ወደ 311 መደወል ወይም ወደ  www.mc311.com ድረ ገጽ መሄድ ይችላሉ።
  • ጥ፡ ስልክ ስደውል ወይም ኢሜል ስልክ ስሜን መስጠት አለብኝ?
  • መ፡ MC311 ከደንበኛ አገልግሎት ተወካይ ሲነጋገሩ ወይም በኢሜል የሚሰጡትን መረጃ ይሰበስባል። እርስዎ የጠየቋቸውን አገልግሎቶች ለማቅረብ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ብቻ ይሰበሰባሉ። MC311 ደዋዮች አስተያየታቸውን ሊሰጡ ወይም አንዳንድ ኣገልግሎቶች እና መረጃዎችን ስም ሳይታወቅ እንዲያገኙ መጠየቅ ይችላሉ።
  • ጥ፡ የተወሰነ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ወደ 311 ሊደውሉ ይችላሉ?
  • መ፡ አዎ። ብዙዎቹ የደንበኞች አገልግሎት ተወካዮች ስፓንኛ ይናገራሉ። በተጨማሪ MC311 የደንበኛ አገልግሎት ማዕከል ከ 150 ቋንቋዎች በላይ የቋንቋ የትርጉም አገልግሎት ይሰጣል።ወደ 311  ሲደውሉ፡ ለስፓኒሽ  (1) ይጫኑ፡ካልሆነ የሚቀጥለውን የደንበኛ አገልግሎት ተወካይ በመረጡት ቋንቋ እንዲደውሉለት ለመጠየቅ መስመር ላይ ይቆዩ። የእኛ የትርጉም አገልግሎት ይቀርብልዎታል።
  • ጥ፡ 311 ን ካገኘሁ በኋላ ምን ይከሰታል?
  • መ፡ የደንበኛው አገልግሎት ተወካይ የጠየቁትን መረጃ ይሰጡዎታል ወይም ደግሞ የአገልግሎት ጥያቄዎን ወደ ተገቢው ክፍል ይልካል። ጥያቄዎን በኦንላይን ወይም በስልክ ጥሪ አማካይነት የጥያቄዎን ሂደት መከታተል እንዲችሉ የአገልግሎት ጥያቄ ቁጥር ይሰጥዎታል።
  • ጥ፡ የMC311 የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል የነዋሪው ጥያቄን ይከታተላልን?
  • መ፡ የ MC311 ተወካዮች የአንድ የአገልግሎት ጥያቄ ሁኔታን መከታተል ይችላሉ፡ ሆኖም ግን ስራው የተሟላ መሆኑን የማረጋገጥ ተግባር የእያንዳንዱ ክፍል ጥያቄውን የያዘው ክፍል ኃላፊነት ነው።
  • ጥ፡ ስልክ ቁጥሩን ካወቅሁ አሁንም በቀጥታ ወደተወሰነ ዲፓርትመንት (ክፍል)  መደወል እችላለሁ?
  • መ፡ አሁንም ወደ ቀጥተኛ ቁጥር መደወል ይችላሉ፡ ነገር ግን ባለፉት ጊዜያት የተጠቀሟቸው 30 የካውንቲ የመንግስት ቁጥሮች ወደ 311 ጥሪ ማዕከል ተላልፈዋል።
  • ጥ፡ በማንኛውም የሞንጐመሪ ካውንቲ ወረዳዎች ውስጥ ባሉ የከተማ ወሰኖች የምኖር ከሆነ ምን ይከሰታል?
  • መ፡ አሁንም ወደ 311 መደወል ይችላሉ። ሆኖ ግን የርስዎ የአገልግሎት ጥያቄ በስልጣናቸው ስር የሚገኝ ከሆነ፡ በአካባቢዎ ወደ ሚገኘውን የወረዳ የመንግስት ቢሮ እንዲደውሉ ሊመሩ ይችላሉ።
  • ጥ፡ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ወይም የሞንትጐመሪ ኮሌጁ መረጃን በሚመለከት ወደ311 መደወል እችላለሁ?
  • መ፡ የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን ወይም የሞንትጐመሪ ኮሌጅን የሚመለከቱ ጥያቄዎች አሁንም ወደ እነዚያ ድርጅቶች በቀጥታ ይሄዳሉ።
  • ጥ፡ ከስራ ሰዓቶች ውጭ ወደ 311ብደውል ምን ይከሰታል?
  • መ፡ የስራ ሰዓቶችን የሚሰጥ እና አስቸኳይ ሁኔታ የተፈጠረ እንደሆነ ወደ 911 ወይም ወደ ክራዚዝ ሰንተር እንዲደውሉ የሚመራዎት የተቀረጸ ድምጽ ይሰማሉ።
  • ጥ፡ በአስቸኳይ ሁኔታስ – 311 የመርዳት ሓላፊነት ይኖራዋል?
  • መ፡ MC311 የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል፡ ከባድ የአየር ሁኔታ፡ የህዝብ ጤና እና የህዝብ ደህንነት ክስተቶችን ጨምሮ ሁሉም የካውንቲ የአደጋ ግብረ መልስ ጥረቶችን ይደፋል።
  • ጥ፡ ወደ 311 በመደወል በህዝብ ችሎት ለመመስከር መመዝገብ እችላለሁን?
  • መ፡ ለሕዝብ ችሎት ምዝገባ ወደሚቀበል ኤጀንሲ ይመራዎታል።
  • ጥ፡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ መንግስት ስለሚኖሩ የስራ ዕድሎች በሚመለከት ወደ 311 መደወል እችላለሁን?
  • መ፡ አዎን። MC311 የደንበኞች አገልግሎት ተወካዮች ለጥያቄዎችዎ መልስ ሊሰጡ እንዲሁም ለካውንቲ ስራ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል የሚገልጹ መመሪያዎችን መስጠት ይችላሉ።
  • ጥ፡ በ 311 በመደወል በካውንቲ ጤና ጥበቃ ክሊኒክ ቀጠሮ መያዝ እችላለሁን?
  • ጥ፡ አይ። ቀጠሮ ለመያዝ ከጤና ማእከል ጋር በቀጥታ መነጋገር ያስፈልጋል። የMC311 ሰራተኞች እነዚህን ጥሪዎች ወደ ተገቢ የጤና ክሊኒክ ያስተላልፋሉ።

የኤምሲ311 (MC311) ገጽታዎች

311 አስቸኳይ ላልሆነ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት መረጃ እና አገልግሎቶች ስልክ ቁጥር ነው። አስቸኳይ ሁኔታን ለሚመለከቱ ጥሪዎች ነዋሪዎች ወደ 911 መደወል ይኖርባቸዋል።

  • 311 ደንበኞች (ነዋሪዎች) የሞንትጐመሪ ካውንቲ መረጃ እና አገልግሎቶችን ለማግኘት በቀላሉ ማስታወስ የሚችሉትን ቁጥር መደወል እንዲኖራቸው ያደርጋል።
  • በተጨማሪም ደንበኞች መረጃዎችን ማግኘት እና በድረ ገጽ፡  www.mc311.com አማካይነት የአገልግሎት ጥያቄዎችን ማቅረብ ወይም መከታተል ይችላሉ።
  • የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ ዓርብ፡ ከጧቱ 7 00 ሰዓት እስከ ምሽቱ ናቸው፡ የ24/7 አገልግሎት ለማግኘት ወደ www.mc311.com ይሂዱ።
  • ስፓኒሽ የሚናገሩ የሰለጠኑ ተወካዮች ይኖራሉ፤ እንዲሁም ለሌሎች ቋንቋዎች የትርጉም አገልግሎትን ጨምሮ።
  • ቲቲዋይ (TTY) ወደ 301-251-4850 በመደወል ይገኛል።
  • የደንበኛ አገልግሎት ተወካዮች እና የኦንላይን ሲስተም የካውንቲ መንግስታዊ መረጃ እና አገልግሎት በሚመለከት በየጊዘው የሚታደስ ዘመናዊ ዳታቤዝ በመጠቀም በጣም ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን መረጃዎችን ያቀርባል።
  • የ 311 ስርዓት እንደ የማህበረሰብ ክስተት / አስቸኳይ ሁኔታ፡ የውኃ ዋና መቋረጥ፡የኤች 1 ኤን 1 (H1N1) ወረርሽኝ ወይም ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዘ አደጋ ሲከሰቱ መረጃዎችን በፍጥነት ሊያካትት ይችላል።

የ MC311 ቁጥሮች

  • በሞንትጐመሪ ካውንቲ ውስጥ ካሉ ወደ 311 ይደውሉ።
  • ከሞንትጐመሪ ውጭ ከሆኑ ወደ 240-777-0311 ይደውሉ።
  • የ ቲቲዋይ (TTY) ቁጥር 301-251-4850 ነው።
ለማስታወስ ያህል: ለአስቸኳይ ሁኔታ ወደ 911 ይደውሉ፡
ድረ ገጽ: www.mc311.com