ንግድ ተቋማትን እንደገና ለመክፈት መሟላት የሚገባቸው
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የንግድ ማህበረሰብ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሰራተኞቹንና የካውንቲ ነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ቁልፍ አጋር ነው፡፡ሁሉም የንግድ ድርጅቶች በእንደገና የመክፈት ወቅት የሚከተሉትን ህጎች ማክበር ይጠበቅባቸዋል ፡፡እነዚህ ሕጎች በሚታይ ቦታ ላይ በመለተፍ ሕዝባዊ ማስጠንቀቅያና ተፈጻሚነታቸውን ያረጋግጡ፡፡
ለህትመት አጠቃላይ የአሰራር መስፈርቶች (እንግሊዝኛ - ፒዲኤፍ)
- በአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ (ሲ.ዲ.ሲ) ወይም በሜሪላንድ የጤና መምሪያ (ኤምዲኤች)፣ ከሁለቱም የበለጠ በጠበቀው፣ መመሪያ መሠረት ማህበራዊ ርቀትን በጥብቅ መከተል ያስፈልጋል።
- ሰራተኞችን እና ደንበኞችን ለመምራት ምልክቶችን እና መጠቆሚያዎችን ይጠቀሙ
- ሁሉም ሰራተኞች እና ከ 2 አመት በላይ የሆኑ ደንበኞች በሙሉ በሲዲሲ ወይም በኤምዲኤች፣ ከሁለቱም የበለጠ በጠበቀው፣ መመሪያ መሰረት የፊት መሸፈኛ እንዲለብሱ ይጠይቁ ።
- ለሥራ ቦታቸው የዘመነው የሲዲሲን (CDC ) መመሪያ የሚያንፀባርቅ ለሠራተኞች መመሪያና ሥልጠና ይስጡ
- በየቀኑ ቦታዎችን ለማፅዳት በሲዲሲ እና በአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ (ኢ.ኢ.ፒ.) የጸደቁ ፀረ-ተባዮችን ይጠቀሙ
- ሰራተኞች እጃቸውን በየሰዓቱ እንዲታጠቡ ይጠይቁ
- የሲዲሲ ፣ የኤምዲኤች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎቶች አዳዲስ መመሪያዎችን እንደደረሰዎ ይመርምሩና ይተግብሩ