ሃሎዊን

ሃሎዊንን ለማክበር የሚደረጉ ብዙ ባህላዊ መንገዶች ሰዎች ከቤተሰብ ውጭ ከሆኑ አባላት ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲቀንሱ አያስችልም ፣ ስለሆነም ኮቪድ -19 ን የማስፋፋት አደጋን ለማስወገድ ቀደም ብሎ ማቀድ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አማራጮችን መለየት አስፈላጊ ነው ፡፡

የ ኮቪድ -19 አካባቢያዊ ትዕዛዝ ከ 50 በላይ ለሆኑ ሰዎች ክንውኖችን ወይም እንቅስቃሴዎችን አይፈቅድም ፡፡ ትልልቅ የሃሎዊን ስብሰባዎች ፣ ከቤት ውጭ ቢካሄዱ እንኳን አይፈቀዱም ፡፡

የማረጋገጫ ደብዳቤ ካልተሰጠ በስተቀር ካርኒቫሎች ፣ ክብረ በዓላት ፣ የቀጥታ መዝናኛዎች እና የቅሬተ ቅርፀ አካል(ጎስት) መስህብ ቤቶች አይፈቀዱም ፡፡ ለፍቃድ ማረጋገጫ ደብዳቤ ያመልክቱ ፡፡

እነዚህን ክንውኖች ያስወግዱ

 • ባህላዊው ፣ ከቤት ወደ ቤት (ትሪክ)ተንኮል -ወይስ-ሥጦታ(ትሪት) ጨዋታ ፤, በበረንዳዎች ና በፊት ለፊት በሮች ላይ ተገቢውን አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ ችግር በመኖሩ
  • ሆኖም ግለሰቦች ይህን የሚያደርጉ ከሆነ እባክዎን መልስ የሚሰጥ ወይም ወደ በሩ የሚመጣ ሰው ሁሉ የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል በተገቢው መልኩ ጭምብል እንዳደረገ የማረጋገጥ ጥረት ያድርጉ ፡፡
 • እንደ “ትራንክ ወይም ትሬቲንግ” ባሉ እንቅስቃሴዎች ምግብ መጋራት ፣ ልጆች ከቤት ወደ ቤት ከመሄድ ይልቅ ከመኪና ወደ መኪና የሚሄዱበት

እኛ የምንመክራቸው እንስቃሴዎች

ለህፃናት እና ለቤተሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ እንዲኖር በዚህ አመት ሃሎዊንን ለማክበር እነዚህን አማራጭ መንገዶች እንመክራለን

 • የኦን ላይን ፓርቲዎች / ውድድሮች (ለምሳሌ አልባሳት ወይም ዱባ መቅረጽ)፣
 • ቤቶችን, ጓሮዎችን እና አከባቢዎችን በሃሎዊን-ገጽታ ማስጌጫዎች ማስጌጥ;
 • የመኪና ሰልፎች እንደ:
  • ድራይቭ ባይ ክንዋኔዎች ወይም ውድድሮች ግለሰቦች ተሽከርካሪዎቻቸውን በሚያለብሱበት ወይም በሚያስጌጡባቸው ውድድሮች ፣ ተገቢውን አካላዊ ርቀት በጠበቁ “ዳኞች”ይከናወናሉ።
  • ድራይቭ ኢን ወይም ድራይቭ ስሩ ክንዋኔዎች ግለሰቦች በተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ የሚቆዩበት ቦታ እና የሃሎዊን ገጽታ ማሳያዎች ባሉበት ቦታዎች መንዳት ፡፡ ተሳታፊዎቹ በተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ እሽግ ስጦታዎችን (ትሬት ባግ) ይቀበላሉ፤ (በንግድ ድርጅቶች የታሸጉ የማይበላሹ ስጦታዎች የተወሰነ) ወይም ሌላ የሚወስዱ ነገሮችን ከአዘጋጁ በመኪናቸው ውስጥ እንዳሉ ማግኘት ይችላሉ
 • የሃሎዊን የፊልም ምሽቶች በድራይቭ ኢን ቲያትሮች (የህዝብ ጤና ድራይቭ-ኢን ፊልም ቲያትር መመሪያን ማክበር አለባቸው)፤
 • ከቤት ውጭ የሚያስተናግዱ ምግብ ቤቶች ውስጥ የሃሎዊን ገጽታ ያላቸው ምግቦች ( ከምግብ ቤቱ ፕሮቶኮል)ጋር መጣጣም አለባቸው)፤ እና
 • በውጭ ሙዚየም ሃሎዊንን ጭብጥ ያደረጉ የሥነ-ጥበባት ሥራዎች (ከሕዝብ ጤና ሙዚየም መመሪያ ጋር መጣጣም አለባቸው) ፡፡

አስተማማኝ የጤና ልምዶች

ሃሎዊንን ለማክበር እንዴት እንደሚመርጡ ምንም ይሁን ምን የሚከተሉትን ማድረግ አስፈላጊ ነው

 • ከቤትዎ ውጭ እና ቤተሰብዎ ባልሆኑ ሌሎች ሰዎች መካከል ሲሆኑ በሽታው እንዳይዛመት ለመከላከል የጨርቅ ፊት መሸፈኛ በትክክል መልበስ ፤
 • እፍግፍግ ያሉ ቦታዎችን ያስወግዱ ፡፡ በእርስዎ እና በሌሎች መካከል ቢያንስ ስድስት ጫማዎችን በቀላሉ ለማለያየት ከማያስችል የቤት ውስጥ ቦታዎች በንቃት ይራቁ;
 • የቀረበ ግንኙነትን ያስወግዱ. የራስዎ ቤተሰብ ካልሆኑ ሰዎች ሁሉ ቢያንስ ስድስት ጫማ ይራቁ ፣ በተለይም ሲያወሩ ፣ ሲበሉ ፣ ሲጠጡ;
 • እጆችዎን ብዙ ጊዜ መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት;
 • ቶሎ ቶሎ የሚነኩ ነገሮችን አዘውትሮ ማጽዳት; እና
 • እርሶ ከታመሙ ወይም በኮቪድ-19 ከታመመ ወይም የ ኮቪድ-19 ምልክቶች ካለበት ሰው ጋር ተገናኝተው ከሆነ በቤትዎ ይቆዩ ከሌሎችም ይራቁ