ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ህጻናት የኮቪድ-19 ክትባቶች

ይህ ይዘት በዲሰምበር 15፣ 2021 ተረጋግጧል

ከ5 እስከ 11 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ልጆች ክትባት በሜሪላንድ ውስጥ ባሉ የአካባቢ ጤና መምሪያዎች፣ የግል የህክምና ተቋማት እና ፋርማሲዎች እየተሰራጨ ነው። ሁለት ሶስተኛው የክትባት መጠን በፋርማሲዎች እና በጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ይሰጣል፤ አንድ ሶስተኛው የሚሆነው ደግሞ Montgomery County Department of Health and Human Services (DHHS) (በሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰው አገልግሎት መምሪያ ) ይሰጣል። ክትባቶችን የሚሰጡ ብዙ ቦታዎች ስላሉ ተጠቃሚ ይሁኑ።

በየሳምንቱ ተጨማሪ የክትባቶች መጠኖችን እናገኛለን። መጀመሪያ ላይ የክትባት መጠኖች ብዛት ውስን ስለሚሆን እባክዎን ይታገሱ። ለክትባቱ ብቁ የሆኑትን ልጆች ሁሉ ወዲያውኑ መከተብ አንችልም። የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ክትባቶችን እየሰጠ እንደሆነ ለማወቅ ያነጋግሩ።

ከ5 እስከ 11 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ከ100,000 በላይ ልጆች እንዳሉን እንገምታለን፡፡ ክትባት የሚፈልጉትን ልጆች ሙሉ በሙሉ ለመከተብ የተወሰነ ጊዜ ይወስዳል።

ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 የሆኑ ህጻናት በ3 ሳምንታት ልዩነት 2 የፋይዘር (Pfizer) የክትባት መጠኖችን ያገኛሉ። የሕፃናት ክትባቱ በልዩ ሁኔታ የታሸገ ነው። ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ከሚሰጠው የፋይዘር (Pfizer) የክትባት መጠን ጋር ሊቀያየረ አይችልም።

ብዙ ቦታዎች የልጆች ክትባት ቀጠሮዎችን እየሰጡ ይገኛሉ

1

የልጅዎን የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ያነጋግሩ

ከ 5 እስከ 11 እድሜ ለሆኑ ልጆች ክትባት የሚሰጡ የአካባቢው ጤና አጠባበቅ አቅራቢዎችን ዝርዝር ይመልከቱ

2

ፋርማሲዎች ጋር ያረጋግጡ

3

በካውንቲው የሚተዳደሩ ክሊኒኮች ጋር ያረጋግጡ

ልጅዎችዎ የኮቪድ-19 ( COVID 19) ክትባትን በማህበረሰብ ክሊኒክ እንዲወስዱ ቀጠሮ መያዝ ይኖርብዎታል። ያለ ቀጠሮ መቀበል አንችልም ፤ ምንም ልዩ ሁኔታዎችን አንቀበልም። በቀኑ መጨረሻ ምንም የተረፈ የክትባት መጠን እንዳይባክን የክሊኒኮቻችንን የክትባት አቅርቦት አቅደናል። 

የልጅዎን የክትባት ቀጠሮ ለመያዝ እርዳታ ከፈለጉ፡ ለኮቪድ-19 ( COVID 19) የጥሪ ማእከል በ240-777-2982 (ከሰኞ እስከ አርብ፡ ከጥዋቱ 9፡00 እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት) ይደውሉ። የኦላይን ቀጠሮዎች ሲሞሉ፣ የጥሪ ማእከሉ ተጨማሪ ቀጠሮዎች አይኖሩትም።

በካውንቲው የሚተዳደር ክሊኒክ ጋር ቀጠሮ ይያዙ

የልጆቻችን ክሊኒኮች ከ5-11 አመት ለሆኑ ልጆች የክትባት መጠን ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህ ክሊኒኮች ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የክትባት መጠኖች ይኖራቸዋል።

ተጨማሪ ክሊኒኮች እና ቀጠሮዎች ሲጨመሩ ወይም ሲከፈቱ ለማየት የጤና እና የሰው አገልግሎት መምሪያን በ @MoCoDHHS በትዊተር እና @mocdhhs በፌስቡክ ላይ ይከተሉ።

ለልጅዎ ቀጠሮ ይዘጋጁ

ልጅዎችዎ ወደ ላይኛው ክንዳቸው በቀላሉ ለመድረስ የሚያሰችሉ ልብሶችን እንዲለብሱ ያድርጉ። ክትባት ለመውሰድ የእጅጌአችውን ልብስ እንዲሰበስቡ እንጠይቃቸዋለን።

ለልጅዎ ቀጠሮ ከ15 ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ አስቀድመው ይድረሱ። ማንኛውም ቀጠሮ ያለው ልጅ በተመዘገበበት ክሊኒክ ውስጥ ክትባቱን እንደሚወስድ ዋስትና ተሰጥቶታል።


ከ 5 እስከ 11 እድሜ ለሆኑ ህፃናት ክትባት ያላቸው የአካባቢዉ ጤና አጠባበቅ አቅራቢዎች

 • Access Now Urgent Care (አክሰስ ናው አስቸኳይ እንክብካቤ)
 • AccessAbility MedCare, LLC (አክሰስኤቢሊቲ ሜዲኬር ፣ LLC)
 • Advanced Neighborhood Pediatrics, LLC - Clarksburg (አድቫንስድ የሕፃናት ሕክምና, LLC - ክላርክስበርግ)
 • Advanced Neighborhood Pediatrics, LLC - Silver Spring (አድቫንስድ የሕፃናት ሕክምና, LLC - ሲልቨር ስፕሪንግ)
 • Bethesda Pediatrics (ቤተስዳ የሕፃናት ሕክምና)
 • Brookville Pharmacy and Wellness Center (ብሩክቪል ፋርማሲ እና ጤና ማእከል)
 • Capital City Primary and Immediate Care (የካፒታል ሲቲ የመጀመሪያ እና ፈጣን እንክብካቤ)
 • Capitol Medical Group (ካፒቶል የሕክምና ቡድን)
 • Capitol Medical Group (ካሳ ሩቢን፣ Inc)
 • Coleman Pediatrics (ኮልማን የሕፃናት ሕክምና)
 • Coleman Pediatrics (ኮምፕሊት እንክብካቤ ለልጆች)
 • Discovery Pediatrics, LLC - 600 Doses (ዲስከቨሪ ሕፃናት ሕክምና, LLC - 600 ዶዝ)
 • Friendship Pediatrics, PA (ፍሬንድ ሽፕ የሕፃናት ሕክምና, ፒኤ)
 • Hashim S. Hashim, MD (ሃሺም ኤስ. ሃሺም፣ ኤም ዲ)
 • Hirsch Pediatrics (ሂርሽ የሕፃናት ሕክምና)
 • Horizon Pediatric, Inc. (ሆራይዘን የህፃናት ህክምና )
 • International Pediatrics, PA - Gaithersburg (ዓለም አቀፍ የሕፃናት ሕክምና፣ ፒኤ ጌይተርስበርግ)
 • John Choi, MD PC (ጆን ቾይ, ኤም ዲ ፒሲ)
 • Kaiser Permanente - Gaithersburg Medical Center (ካይዘር ፐርመነቴ : ጌይተርስበርግ የሕክምና ማዕከል)
 • Kelly Goodman, NP and Associates, PC (ኬሊ ጉድማን፣ ኤን እና ተባባሪዎች, ፒሲ)
 • Kenwood Pediatrics Center (ኬንውድ የሕፃናት ሕክምና ማዕከል)
 • Maryland Pediatric Care LLC (የሜሪላንድ የሕፃናት ሕክምና LLC)
 • Medstar Medical Group at Forest Hill (ሜድስታር ሜድካል ግሩፕ በፎረስት ሂል)
 • MedStar Medical Group Pediatrics at Olney (ሜድስታር ሜድካል ግሩፕ የሕፃናት ሕክምና በኦልኒ)
 • Montgomery Medical Clinic - KESSOUS (የሞንትጎመሪ የሕክምና ክሊኒክ፟፤ ኬሱስ)
 • Olney Pediatrics (ኦልኒ የሕፃናት ሕክምና)
 • Park Pediatrics - Takoma Park (ፓርክ የሕፃናት ሕክምና - ታኮማ ፓርክ)
 • Pediatric and Adolescent Care of Silver Spring (የሕፃናት እና የአዶለሰንት እንክብካቤ, ሲልቨር ስፕሪንግ )
 • Pediatric and Adolescent Care, PA (የሕፃናት እና የአዶለሰንት እንክብካቤ, ፒኤ )
 • Pediatric Associates of Montgomery County, PA - Olney (የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፣ ፒኤ -ኦልኒ የሕፃናት ሕክምና ባለሙያዎች)
 • Pediatric Associates of Montgomery County, PA - Rockville (የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፣ ፒኤ -ሮክቪል የሕፃናት ሕክምና ባለሙያዎች)
 • Pediatric Associates of Montgomery County, PA - Silver Spring (የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፣ ፒኤ -ሲልቨር ስፕሪንግ የሕፃናት ሕክምና ባለሙያዎች)
 • Pediatric Associates of Montgomery County, PA - Wheaton (የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፣ ፒኤ -ዊተን የሕፃናት ሕክምና ባለሙያዎች)
 • Pediatric Care ( የሕፃናት ሕክምና)
 • Potomac Valley Pediatrics (የፖቶማክ ቫሊ የሕፃናት ሕክምና)
 • Prime Pediatrics (ፕራይም የሕፃናት ሕክምና)
 • Privia MG - Abdow Friendship Pediatrics (ፕራይቫ ኤም ጂ አብዶው ፍሬንድሽፕ የሕፃናት ሕክምና)
 • Privia MG - Marshak Medical Group (ፕራይቫ ኤም ጂ ማርሻክ የሕክምና ቡድን)
 • Rainbow Pediatric Clinic (ሬንቦ የሕፃናት ሕክምና ክሊኒክ)
 • Rehoboth Medical Center LLC (ሮሆቦት የሕክምና ማዕከል LLC)
 • Right Care Pediatrics (ራይት ኬር የሕፃናት ሕክምና0
 • Saba Pediatric Medicine, LLC ( ሳባ የሕፃናት ሕክምና, LLC)
 • Shady Grove Pediatric Associates (ሼዲ ግሮቭ የሕፃናት ሕክምና ባለሙያዎች)
 • Silver Spring Pediatrics (ሲልቨር ስፕሪንግ የሕፃናት ሕክምና)
 • Smita Parikh Mengers, MD FAAP (ስሚታ ፓሪክ፣ መንገርስ፣ ኤም.ዲ፣ አፋኤኤፒ)
 • Sunshine Pediatrics (ስፕሪንግ የሕፃናት ሕክምና, Inc)
 • Sunshine Pediatrics (ሰን ሻይን የሕፃናት ሕክምና)
 • Theodore F Wells-Green, MD (ቴዎዶር ኤፍ ዌልስ-ግሪን, ኤም.ዲ)
 • Toseg Medical Center (ቶስግ የሕክምና ማዕከል)
 • Virgo-Carter Pediatrics (ቪርጎ-ካርተር የሕፃናት ሕክምና)
 • Washington International Pediatrics (ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ የሕፃናት ሕክምና)
 • White Oak Pediatrics - Gaithersburg (ኃይት ኦክ የሕፃናት ሕክምና - ጋይተርስበርግ)
 • White Oak Pediatrics - Silver Spring (ኃይት ኦክ የሕፃናት ሕክምና - ሲልቨር ስፕሪንግ)
 • Wonder Years Pediatrics (ዎንደር ይርስ የሕፃናት ሕክምና)
 • Xpress Pediatrics Urgent Care Center (ኤክስፕረስ የሕፃናት ሕክምና አስቸኳይ እንክብካቤ ማዕከል)